ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።
ሆሴዕ 1:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ሕዝብና የእስራኤል ሕዝብ እንደ ገና አንድ ይሆናሉ፤ አንድ መሪም ይሾማሉ፤ አንድ ሆነውም በምድሪቱ ይገንናሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ አንድ ይሆናሉ፤ ሁለቱንም የሚያስተዳድር አንድ መሪ ይመርጣሉ፤ እንደገናም በገዛ ምድራቸው ላይ በዕድገትና በብልጽግና ይኖራሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ ለእነርሱም አንድ አለቃ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና። |
ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።
መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤ ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤ ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል፤ አለዚያማ ደፍሮ፣ ወደ እኔ የሚቀርብ ማን ነው?’ ይላል እግዚአብሔር።
እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቧል፤ እነርሱም ይወርሷታል’ ይላል እግዚአብሔር።”
“ነገር ግን ከዚያ ጊዜ በኋላ፣ ከእስራኤል ቤት ጋራ የምገባው ኪዳን ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሕጌን በአእምሯቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ። እኔ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
‘በጽኑ ቍጣዬና በታላቅ መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁበት ምድር ሁሉ በእውነት እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ ያለ ሥጋትም እንዲቀመጡ አደርጋቸዋለሁ።
“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ያዕቆብን አሁን ከስደት እመልሰዋለሁ፤ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እራራለሁ፤ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀናለሁ።
ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው አምላካቸውን እግዚአብሔርንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በመጨረሻውም ዘመን በመንቀጥቀጥ ወደ እግዚአብሔርና ወደ በረከቱ ይመጣሉ።