ዘፍጥረት 50:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን፣ “እነሆ፤ የመሞቻዬ ጊዜ ተቃርቧል፤ እግዚአብሔርም በረድኤቱ ይጐበኛችሁና ከዚህ አገር ያወጣችኋል፤ ለአባቶቻችን ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባችኋል” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ወንድሞቹን፦ “እኔ እሞታለሁ፥ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፥ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተን ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጐበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደ ገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ወንድሞቹን አላቸው፥ “እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም መጐብኘትን ይጐበኛችኋል፤ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል። ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያገባችኋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ወንድሞቹን አለ፦ እኔ እሞታለሁ እግዚአብሔር መጎብኘትን ይጎበኛችኍል ከዚህችም ምድር ያወጣችኍል ለአብርሃምን ለይስሕቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኍል። |
በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
ይህችን አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።”
ለጥቂት ጊዜ እዚሁ አገር ተቀመጥ፤ እኔም ካንተ ጋራ እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘርህ በመስጠት ለአባትህ ለአብርሃም በመሐላ የገባሁለትን ቃል አጸናለሁ።
እግዚአብሔርም ከጫፉ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፤ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ።
እስራኤልም የሚሞትበት ጊዜ መቃረቡን እንደ ተረዳ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ እጅህን በጭኔ ላይ አኑረህ፣ በጎነትንና ታማኝነትን ልታደርግልኝ ቃል ግባልኝ፤ በምሞትበት ጊዜ በግብጽ አትቅበረኝ፤
ከዚህ በኋላ እስራኤል ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቧል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሆናል፤ ወደ አባቶቻችሁም ምድር መልሶ ያገባችኋል።
‘የምሞትበት ጊዜ ስለ ተቃረበ፣ በከነዓን ምድር ራሴ ቈፍሬ በአዘጋጀሁት መቃብር እንድትቀብረኝ’ ሲል አባቴ አስምሎኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ልቅበር፤ ከዚያም እመለሳለሁ።”
ዮሴፍ፣ “እግዚአብሔር በርግጥ ይጐበኛችኋል፤ በዚያ ጊዜም ዐፅሜን ይዛችሁ ከዚች ምድር መውጣት አለባችሁ” ብሎ የእስራኤልን ልጆች አስምሏቸው ስለ ነበር ሙሴ የዮሴፍን ዐፅም ይዞ ወጣ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ዙሪያ በሆነው በምድረ በዳው መንገድ ወደ ቀይ ባሕር መራቸው፤ እስራኤላውያንም ለጦርነት ዝግጁ ሆነው ከግብጽ ወጡ።
ስለዚህም ከግብጻውያን እጅ ልታደጋቸውና ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ሰፊና ለም ወደሆነችው ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ፌርዛውያን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ላወጣቸው ወርጃለሁ።
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “አንተና ከግብጽ ያወጣኸው ሕዝብህ ይህን ስፍራ ለቅቃችሁ ‘ለዘርህ እሰጣለሁ’ በማለት ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ተስፋ ወደ ገባሁላችሁ ምድር ሂዱ።
ዳገት መውጣት ሲያርድ፣ መንገድም ሲያስፈራ፣ የአልሙን ዛፍ ሲያብብ፣ አንበጣም ራሱን ሲጐትት፣ ፍላጎት ሲጠፋ፤ በዚያም ጊዜ ሰው ወደ ዘላለማዊ ቤቱ ይሄዳል፤ አልቃሾችም በአደባባዮች ይዞራሉ።
‘በፍጹም ልባቸው ስላልተከተሉኝ ከግብጽ ከወጡት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች አንዳቸውም ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ልሰጥ በመሐላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩዋትም፤
ስለዚህ ኀጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ ሁሉ፣ ሞትም በኀጢአት በኩል ገብቷል፤ በዚሁ መንገድ ሞት ወደ ሰዎች ሁሉ መጣ፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤
እነሆ፤ ይህችን ምድር ሰጥቻችኋለሁ፤ እንግዲህ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ፣ ከእነርሱም በኋላ ለዘሮቻቸው ሊሰጥ የማለላቸውን ምድር ገብታችሁ ውረሱ።”
አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ሲያስገባህ፣ በዚያም ያልሠራሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞችን፣
እስራኤላውያን ከግብጽ ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም፣ ያዕቆብ ከሰኬም አባት ከኤሞር በመቶ ሰቅል ብር በገዛው በሴኬም ምድር ተቀበረ፤ ይህችም የዮሴፍ ዘሮች ርስት ሆነች።