ዘፍጥረት 49:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይሥሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ፥ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ፥ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምና ሚስቱ ሣራ፥ ይስሐቅና ሚስቱም ርብቃ የተቀበሩት እዚያ ነው፤ እኔም ልያን የቀበርኳት እዚያው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምንና ሚስቱ ሣራንም በዚያ ቀበሩአቸው፤ ይስሐቅንና ሚስቱ ርብቃንም በዚያ ቀበሩአቸው፤ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኍት፤ |
አስከሬኑን ወደ ከነዓን ምድር ወስደው አብርሃም ከኬጢያዊው ከኤፍሮን ላይ ከነዕርሻው በገዛው፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ በሚገኘው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።