የምድያም ነጋዴዎችም እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሱ፣ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ጥሬ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
ዘፍጥረት 49:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥንት ተራሮች በረከት፣ ከዘላለም ኰረብቶች ምርቃት ይልቅ፣ የአባትህ በረከት ይበልጣል። ይህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮረብቶችም በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፥ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥንት ጀምሮ ጸንተው ከሚኖሩት ተራራዎችና ዘለዓለማውያን ከሆኑት ኮረብታዎችም ከሚገኘው ደስ ከሚያሰኝ በረከት ሁሉ የአባትህ በረከት ይበልጣል። እንግዲህ ይህ ሁሉ በረከት በዮሴፍ ራስ ላይ ይሁን፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም በዮሴፍ አናት ላይ ይውረድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባትህና የእናትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ይበልጣሉ፤ ዘለዓለማውያን ከሆኑ ከኮረብቶችም በረከቶች ይልቅ ኀያላን ናቸው፤ እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ራስ አናት ላይ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኅያላን ናቸው፤ ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮርፍቶች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ። |
የምድያም ነጋዴዎችም እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሱ፣ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ጥሬ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
ወንድሞቹም፣ “ለካስ በላያችን ለመንገሥ ታስባለህና! ለመሆኑ አንተ እኛን ልትገዛ!” አሉት፤ ስለ ሕልሙና ስለ ተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት።
ተራሮች ቢናወጡ፣ ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤ የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም” ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።
እናንተ በቃሉ የምትንቀጠቀጡ፣ ይህን የእግዚአብሔር ቃል ስሙ፤ “እናንተ ወንድሞቻችሁ የጠሏችሁ፣ ስለ ስሜም አውጥተው የጣሏችሁ፣ ‘እስኪ እግዚአብሔር ይክበርና፣ የእናንተን ደስታ እንይ!’ አሏችሁ፤ ይሁን እንጂ ማፈራቸው አይቀርም።
ቆመ፤ ምድርን አንቀጠቀጠ፤ ተመለከተ፤ ሕዝቦችን አብረከረከ፤ የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ፤ የጥንት ኰረብቶችም ፈራረሱ፤ መንገዱ ዘላለማዊ ነው።