ዘፍጥረት 49:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት፤ በጥላቻም ነደፉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስተኞች አስቸገሩት፥ ነደፉትም፥ ተቃወሙትም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀስተኞቹ በብርቱ ያጠቁታል፤ በቀስታቸውም እየነደፉ ያሳድዱታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምክራቸው የሰደቡት ጌቶች ሆኑበት፤ ቀስተኞችም ወጉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀስተኞች አስቸገሩት ነደፋትም ተቃወሙትም ነገር ግም ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፤ |
የምድያም ነጋዴዎችም እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሱ፣ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ጥሬ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
እርስ በርሳቸውም፣ “ይኸው በወንድማችን ላይ ባደረስነው በደል ምክንያት ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማፀነን፣ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።
የደቀ መዛሙርቱንም ልብ በማበረታታትና በእምነታቸው ጸንተው እንዲኖሩ በመምከር፣ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ማለፍ አለብን” አሏቸው።