ዘፍጥረት 47:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ በግብጽ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ዕድሜውም አንድ መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም በግብጽ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀመጠ፥ የያዕቆብም የሕይወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ዐሥራ ሰባት ዓመት በግብጽ አገር ኖረ፤ ዕድሜውም መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆኖት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም በግብፅ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀመጠ፤ የያዕቆብም መላው የሕይወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም በግብፅ ምድር አሥራ ሰባት ዓመት ተቀመጠ የያዕቆብም ሙላው የሕይወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነው። |
የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረ ጊዜ፣ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋራ የአባቱን በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር። እርሱም ስለ ወንድሞቹ ድርጊት ለአባቱ መጥፎ ወሬ ይዞለት መጣ።
የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን።