ዘፍጥረት 43:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፣ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፥ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ እስከ አሁን ሁለት ጊዜ እዚያ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባንዘገይስ ኖሮ አሁን ሁለተኛ ጊዜ በተመለስን ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባንዘገይስ ኖሮ አሁን ሁለተኛ ጊዜ በተመለስን ነበር። |
ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና አልሙን በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።
ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኀላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘላለም በደለኛው እኔ ልሁን።