ዘፍጥረት 37:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ፤ አሻግረው ሲመለከቱም ከገለዓድ የሚመጡ እስማኤላውያን ነጋዴዎች የግመል ጓዝ አዩ። ነጋዴዎቹ ሽቱ፣ በለሳን ከርቤ በግመሎቻቸው ጭነው ወደ ግብጽ የሚወርዱ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምግብ ሊበሉ ተቀመጡ፥ ዓይናቸውንም አንሥተው ሲያዩ፥ እነሆ የእስማኤላውያን ነጋዴዎች ወደ ግብጽ ለመውረድ ከገለዓድ ይመጣሉ፥ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን፥ ከርቤም ተጭነው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ምሳ ለመብላት ተቀመጡ፤ በሚመገቡበትም ጊዜ እስማኤላውያን ነጋዴዎችን በሩቅ አዩ፤ እነርሱም በግመሎቻቸው ቅመማ ቅመም፥ በለሳን፥ ከርቤም ጭነው ከገለዓድ ወደ ግብጽ የሚጓዙ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንጀራም ሊበሉ ተቀመጡ፤ ዐይኖቻቸውንም በአነሡ ጊዜ እነሆ፥ ይስማኤላውያን ነጋድያን ከገለዓድ ሲመጡ አዩ፤ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን፥ ከርቤም ተጭነው ነበር። ወደ ግብፅ ሀገርም ሊያራግፉ ይሄዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጀራም ሊበሉ ተቀመጡ ዓይናቸውንም አንሥተው አዩ፥ እነሆም የእስማኤላውያን ነገዶች ወደ ግብፅ ለመውረድ ከገለዓድ መጡ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን ከርቤም ተጭነው ነበር። |
የምድያም ነጋዴዎችም እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሱ፣ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ጥሬ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ወደ ግብጽ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖን ሹማምት አንዱ የሆነውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብጻዊው ጲጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው።
ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና አልሙን በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።
መልእክተኞቹ በንጉሡ ትእዛዝ ተቻኵለው ወጡ፤ ዐዋጁም በሱሳ ግንብ ተላለፈ። ንጉሡና ሐማ ለመጠጣት ተቀመጡ፤ የሱሳ ከተማ ግን ግራ ተጋብታ ነበር።
እኅቴ ሙሽራዬ፣ ወደ አትክልት ቦታዬ መጥቻለሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋራ ሰብስቤአለሁ፤ የማር እንጀራዬን ከነወለላው በልቻለሁ፤ ወይኔንና ወተቴንም ጠጥቻለሁ። ወዳጆች ሆይ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እናንተ ፍቅረኞች ሆይ፤ እስክትረኩ ጠጡ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት እንዲህ ይላል፤ “አንተ ለእኔ እንደ ገለዓድ፣ እንደ ሊባኖስ ተራራ ጫፍ ውብ ብትሆንም፣ በርግጥ እንደ ምድረ በዳ፣ ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች አደርግሃለሁ።
“ድንግሊቱ የግብጽ ሴት ልጅ ሆይ፤ ወደ ገለዓድ ውጪ፤ የሚቀባ መድኀኒትም አምጪ፤ ነገር ግን መድኀኒት የምታበዢው በከንቱ ነው፤ ፈውስ አታገኚም።
በምሥራቅ በኩል ወሰኑ በሐውራንና በደማስቆ መካከል፣ በገለዓድና በእስራኤል ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል፤ የምሥራቁ ድንበር እስከ ምሥራቁ ባሕር ይወርድና እስከ ታማር ይዘልቃል፤ ይህም የምሥራቁ ወሰን ይሆናል።