ዘፍጥረት 36:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮባብም ሞተ፥ በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሻም ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮባብም በሞተ ጊዜ የቴማን አገር ተወላጅ ሑሻም በእርሱ እግር ተተክቶ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮባብም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የቴማኒው ሀገር ሑሳም ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሳም ነገሠ |
ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣
ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዳዶስ፣ ናዕማታዊውም ሶፋር በኢዮብ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ሄደው ሊያስተዛዝኑትና ሊያጽናኑት በመስማማት ከየመኖሪያቸው በአንድነት መጡ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ክንዴን በኤዶም ላይ አነሣለሁ፤ ሰዎቹንና እንስሶቻቸውን እገድላለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማንም ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።