ላባም፣ “ታዲያ ምን ልስጥህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ምንም አትስጠኝ፤ ነገር ግን የምጠይቅህን አንዲት ነገር ብቻ ብታደርግልኝ ከብቶችህን ማገዴን እቀጥላለሁ፤
ዘፍጥረት 30:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንጎቹ መካከል ዛሬ ልዘዋወርና ከበጎቹ መካከል ዝንጕርጕር የሆኑትን፣ ነቍጣ ያለባቸውንና ጥቋቍሮቹን እንዲሁም ከፍየሎቹ ነቍጣ ያለባቸውንና ዝንጕርጕሮቹን ልምረጥ፤ እነዚህ ደመወዜ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬ በመንጎችህ በኩል አልፋለሁ፥ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለበቱን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቁጣና ዝንጉርጉር ያለበቱን እለያለሁ፥ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጒርጒርና ነቊጣ፥ ጥቊርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቊጣና ዝንጒርጒር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬ በጎችህ ሁሉ ይለፉ፤ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለበትን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቍጣና ዝንጕርጕር ያለበትን ለይልኝ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬ በመንጎችህ በኩል አልፋለሁ፥ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጉርጉርና ነቍጣ ያለበቱን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቍጣና ዝንጕርጕር እለያለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ። |
ላባም፣ “ታዲያ ምን ልስጥህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ምንም አትስጠኝ፤ ነገር ግን የምጠይቅህን አንዲት ነገር ብቻ ብታደርግልኝ ከብቶችህን ማገዴን እቀጥላለሁ፤
ወደ ፊት ደመወዜን ለመቈጣጠር በምትመጣበት ጊዜ ታማኝነቴ ይታወቃል፤ በመንጎቼ መካከል ዝንጕርጕር ወይም ነቍጣ የሌለበት ፍየል ወይም ጥቍር ያልሆነ በግ ቢገኝ ያ እንደ ተሰረቀ ይቈጠር።”
ነገር ግን በዚያ ዕለት ከተባዕት ፍየሎች ሽመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቍጣ ያለባቸውን ሁሉ፣ እንዲሁም ከእንስት ፍየሎች ነቍጣ ያለባቸውን ዝንጕርጕር የሆኑትን ሁሉ፣ ማንኛውንም ነጭ ያለበትን ሁሉ መረጠ፤ ደግሞም ጥቋቍር የሆኑትንም በጎች ሁሉ ለየና ወንዶች ልጆቹን አስጠበቃቸው።
“እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት፣ የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች መልካቸው፣ ሽመልመሌ፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ዐይኔን አንሥቼ በሕልሜ አየሁ።
እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጕርጕሮቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤