እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፤ “ሁለት ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” አላት።
ዘፍጥረት 27:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ይሥሐቅ ክፉኛ እየተንቀጠቀጠ፣ “ታዲያ ቀደም ሲል ዐድኖ ያመጣልኝ ማን ነበር? አንተ ከመምጣትህ በፊት በልቼ መረቅሁት፤ እርሱም በርግጥ የተባረከ ይሆናል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ “ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም፥ እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅም እጅግ ደንግጦ እየተንቀጠቀጠ “ታዲያ፥ አውሬ አድኖ ያመጣልኝ ማን ነበር? ልክ አንተ ከመምጣትህ በፊት ተመገብኩ፤ የመጨረሻ ምርቃቴንም ሰጠሁት፤ ምርቃቱም የእርሱ ሆኖ ይኖራል” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ፤ እንዲህም አለ፥ “ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣው ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ፤ ባረክሁትም፤ እርሱም የተባረከ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፤ “ሁለት ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” አላት።