በማግስቱም አብርሃም ማልዶ ተነሣ። ጥቂት ምግብ ወስዶ፣ ውሃ በእርኮት አድርጎ ለአጋር ሰጣት፤ በትከሻዋም አሸክሟት ከነልጇ አሰናበታት። እርሷም ሄደች፤ በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ትንከራተት ጀመር።
ዘፍጥረት 26:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም የውሃውን ጕድጓድ ሳቤህ አለው፤ ከዚያም የተነሣ የከተማዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምዋንም “ሳቤህ” ብሎ ጠራት፥ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም የውሃውን ጒድጓድ “ሳቤህ” ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ “ቤርሳቤህ” እየተባለ ይጠራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስምዋንም “መሐላ” ብሎ ጠራት፤ ስለዚህም የከተማዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ዐዘቅተ መሐላ” ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስምዋንም ሳቤህ ብሎ ጠራት ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ነው። |
በማግስቱም አብርሃም ማልዶ ተነሣ። ጥቂት ምግብ ወስዶ፣ ውሃ በእርኮት አድርጎ ለአጋር ሰጣት፤ በትከሻዋም አሸክሟት ከነልጇ አሰናበታት። እርሷም ሄደች፤ በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ትንከራተት ጀመር።
እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ መሆኑን በግልጽ ተረድተናል፤ ስለዚህም፣ ‘በመሐላ የጸና ውል በመካከላችን መኖር አለበት’ አልን፤ ይህም በእኛና በአንተ መካከል የሚጸና ውል ነው፤ አሁንም ከአንተ ጋራ ስምምነት እናድርግ፤