ዘፍጥረት 25:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም በጠቅላላው መቶ ሰባ ዐምስት ዓመት ኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም በሕይወት የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሰባ አምስት ዓመታት ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአብርሃም ዕድሜ በአጠቃላይ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም የኖረበት የዕድሜው ዓመታት እነዚህ ናቸው፤ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም የኖረበት የዕድሜው ዓመታት እነዚህ ናቸው መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ። |
ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋራ ሲነጻጸር ዐጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት።
ዮሴፍም በመቶ ዐሥር ዓመቱ ሞተ፤ ሬሳው እንዳይፈርስ በአገሩ ደንብ በመድኀኒት ከደረቀ በኋላ፣ ሣጥን ውስጥ አስገብተው በግብጽ ምድር አስቀመጡት።