ዘፍጥረት 25:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ እርሱም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ። ዔሳው ብኵርናውን እንዲህ አድርጎ አቃለላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዓይነት ዔሳው ብኩርናውን አቃለላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኲርናውን በመናቅ አቃለላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ንፍሮ ሰጠው፤ በላ፥ ጠጣ፥ ተነሥቶም ሄደ፤ ዔሳውም ብኵርናውን አቃለላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራን የምስር ወጥ ሰጠው በላ ጠጣ ተነሥቶም ሄደ፤ እንዲሁም ዔሳው ብኵርናውን አቃለላት። |
ለሰው፣ ከፀሓይ በታች ከመብላት፣ ከመጠጣትና ከመደሰት ሌላ የተሻለ ነገር ስለሌለ፣ በሕይወት ደስ መሠኘት መልካም ነው አልሁ፤ ስለዚህ አምላክ ከፀሓይ በታች በሰጠው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሥራው ደስታ ይኖረዋል።
ነገር ግን እነሆ፤ ደስታና ሐሤት፣ ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ! “ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፤ እንጠጣ!” አላችሁ።
እግዚአብሔርም ሊከፍሉኝ የተስማሙበትን ጥሩ ዋጋ “በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው” አለኝ፤ እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በእግዚአብሔር ቤት ባለው ግምጃ ቤት አስቀመጥሁት።
በኤፌሶን ከአራዊት ጋራ የታገልሁት ለሰብኣዊ ተስፋ ብቻ ከሆነ ትርፌ ምንድን ነው? ሙታን የማይነሡ ከሆነ፣ “ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፤ እንጠጣ፤” እንደሚሉት መሆናችን ነው።