ስለ እስማኤልም ቢሆን ልመናህን ሰምቼሃለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ የዐሥራ ሁለት አለቆች አባት ይሆናል፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ።
ዘፍጥረት 25:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስማኤል ልጆች ስም እንደ ዕድሜያቸው ቅደም ተከተል እንዲህ ነው፦ የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በትውልዳቸው ቅደም ተከተል የተዘረዘሩት የእስማኤል የልጆቹ ስም እንዲህ ነው፥ የእስማኤል የበኩር ልጁ ነባዮት፥ እና ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፥ ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውና በየትውልዳቸው እንዲህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውን በየትውልዳቸው እንዲህ ነው፤ የእስማኤል የበኵር ልጁ፥ |
ስለ እስማኤልም ቢሆን ልመናህን ሰምቼሃለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ የዐሥራ ሁለት አለቆች አባት ይሆናል፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እኔ ጥቍር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ ጥቍረቴ እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣ እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎችም ነው።
ምድረ በዳውና ከተሞቹ ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ፤ ቄዳር ያለችበት መንደር ደስ ይበለው፤ የሴላ ሕዝቦች በደስታ ይዘምሩ፤ ከተራሮችም ራስ ላይ ይጩኹ።
የቄዳር የበግ መንጋ ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባል፤ የነባዮት አውራ በጎች ያገለግሉሻል። እነዚህም በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸው መሥዋዕቶች ይሆናሉ፤ እኔም የክብር መቅደሴን ግርማ አጐናጽፈዋለሁ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ወጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት የተነገረ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተነሡ፣ ቄዳርን ውጉ፤ የምሥራቅንም ሕዝብ ደምስሱ።
እርሱም፣ “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁ ከምርኮ ካገኛችሁት ውስጥ የጆሮ ጕትቻችሁን እንድትሰጡኝ ነው” አላቸው፤ የወርቅ ጕትቻ ማድረግ የእስማኤላውያን ባህል ነበርና።