ስለ እስማኤልም ቢሆን ልመናህን ሰምቼሃለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ የዐሥራ ሁለት አለቆች አባት ይሆናል፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ።
ዘፍጥረት 25:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብጻዊቷ የሣራ አገልጋይ አጋር፣ ለአብርሃም የወለደችለት የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሣራ አገልጋይ ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችው የአብርሃም ልጅ የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሣራ አገልጋይ ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሣራ ባሪያ ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት የአብርሃም ልጅ የይስማኤል ትውልድ ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሣራ ባሪያ ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችው የአብርሃም ልጅ የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው፤ |
ስለ እስማኤልም ቢሆን ልመናህን ሰምቼሃለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ የዐሥራ ሁለት አለቆች አባት ይሆናል፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ።
እርሱም፣ “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁ ከምርኮ ካገኛችሁት ውስጥ የጆሮ ጕትቻችሁን እንድትሰጡኝ ነው” አላቸው፤ የወርቅ ጕትቻ ማድረግ የእስማኤላውያን ባህል ነበርና።