ዘፍጥረት 23:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም እየሰሙት ኤፍሮንን፣ “የዕርሻውን ቦታ ዋጋ ልክፈል፤ እባክህን ተቀበለኝና ሬሳዬን ልቅበርበት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ፈቃድህ ከሆነ፥ አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ፥ አንተም ከእኔ ተቀበለኝና የሚስቴን አስክሬን እዚያ ወስጄ ልቅበር” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም እየሰሙ ዔፍሮንን “እባክህ አድምጠኝ፤ ቦታውን በሙሉ እገዛዋለሁ፤ እነሆ ዋጋውን ተቀበለኝና የሚስቴን አስከሬን እዚያ ወስጄ ልቅበር” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሀገሩ ሕዝብም ሲሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “ከእኔ ቅርብ ነህና ስማኝ፤ የእርሻህንም ዋጋ ከእኔ ውሰድ፤ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአገሩ ሰዎችም ሲሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ ነገሬን ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፥ ሬሳዬም፥ በዚይ እቀብራለሁ። |
ንጉሡ ግን ኦርናን፣ “እንዲህ አይደረግም፤ ዋጋውን ላንተ መክፈል አለብኝ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በዐምሳ ሰቅል ብር ገዛ፤
በጕልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ምስጉን ነው’ ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ።”