ዘፍጥረት 18:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሣራ ስለ ፈራች፣ “ኧረ አልሣቅሁም” ብላ ዋሸች። እርሱ ግን፣ “ሣቅሽ እንጂ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሣራም ስለ ፈራች፦ “አልሳቅሁም” ስትል ካደች። እርሱም፦ “አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሣራ እጅግ ፈርታ ስለ ነበር “አልሳቅሁም” ብላ ካደች። እርሱ ግን “በእርግጥ ስቀሻል” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሣራም ስለ ፈራች “አልሳቅሁም” ብላ ካደች። እርሱም፥ “አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሣራ፥ ስለ ፈራች፤ አልሳቅሁም ስትል ካደች። እርሱም፤ አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ አላት። |
እርሱም፣ “አነጋገርሽ እንደ ሞኝ ሴት ነው፤ መልካሙን ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀበልን፤ ክፉውንስ አንቀበልምን? አላት።” በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ በንግግሩ አልበደለም።