የእግዚአብሔርም መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ ፀንሰሻል፤ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ፤ እግዚአብሔር ችግርሽን ተመልክቷል፤ ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ።
ዘፍጥረት 16:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አጋር ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ አብራምም ስሙን እስማኤል ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፥ አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አጋር ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ እርስዋ የወለደችለትንም ልጅ “እስማኤል” ብሎ ስም አወጣለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ አጋር ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን የሕፃኑን ስም ይስማኤል ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው። |
የእግዚአብሔርም መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ ፀንሰሻል፤ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ፤ እግዚአብሔር ችግርሽን ተመልክቷል፤ ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ።
ስለ እስማኤልም ቢሆን ልመናህን ሰምቼሃለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ የዐሥራ ሁለት አለቆች አባት ይሆናል፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ።
ከዚህ ይልቅ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች እንሽጠው፤ እጃችንን ግን በርሱ ላይ አናንሣ። ምንም ቢሆንኮ ወንድማችን፣ ሥጋችን ነው” ወንድሞቹም በሐሳቡ ተስማሙ።