ዕዝራ 8:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ከሴኬንያ ዘሮች ነው፤ ከፋሮስ ዘሮች ዘካርያስና ከርሱም ጋራ 150 ወንዶች ተመዝግበው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሽካንያ ልጆች፥ ከፓርዖሽ ልጆች ዘካርያስና፥ ከእርሱም ጋር መቶ ሃምሳ ወንዶች ተመዝግበው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሴኬንያ ልጆች፥ ከፋሮስ ልጆች ዘካርያስ፥ ከእርሱም ጋር የተቈጠሩ መቶ አምሳ ወንዶች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፋሮስ ልጆቾ ዛካርያስ፥ ከእርሱም ጋር መቶ አምሳ ወንዶች በትውልድ ተቈጠሩ። |