ዕዝራ 4:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደብዳቤው የተጻፈው፣ ከአገረ ገዥው ሬሁም፣ ከጸሓፊው ሲምሳይ በትሪፖሊስ፣ በፋርስ፣ በአርክ፣ በባቢሎን እንዲሁም በሱሳ ማለትም በኤላማውያን ላይ ዳኞችና ገዦች ከሆኑት ከተባባሪዎቻቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዛዡ ሬሑምና ጸሐፊው ሺምሻይ የቀሩትም ተባባሪዎቻቸው፥ ዳኞቹ፥ ባለሥልጣኖቹ፥ አስተዳዳሪዎቹ፥ ጸሐፍያን፥ የኤርካውያን፥ ባቢሎናውያን፥ ሱሳንካውያን፥ ዴሐውያን፥ ዔላማውያን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአገረገዢ ረሑምና ከአውራጃው ጸሐፊ ሺምሻይ፥ እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ከሆኑት ዳኞችና ቀድሞ በዔላም ምድር በኤሬክ፥ በባቢሎንና በሱሳ ይኖሩ ከነበሩት ሌሎችም ባለ ሥልጣኖች ሁሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዛዡ ሬሁም፥ ጸሓፊውም ሲምሳይ፥ የቀሩትም ተባባሪዎቻቸው፥ ዲናውያን፥ አፈርሳትካዋያን፥ ጠርፈላውያን፥ አፈርሳውያን፥ አርካውያን፥ ባቢሎናውያን፥ ሱስናካውያን፥ ዴሐውያን፥ ኤላማውያን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዛዡ ሬሁም እና ጸሐፊው ሲምሳይ፥ የቀሩትም ተባባሪዎቻቸው፥ ዲናውያን፥ አፈርሳትካውያን፥ ጠርፈላውያን፥ አፈርሳውያን፥ አርካውያን፥ ባቢሎናውያን፥ ሱስናካውያን፥ ዴሐውያን፥ ኤላማውያን፥ |
የአሦርም ንጉሥ ሕዝቡን ከባቢሎን፣ ከኩታ፣ ከአዋና ከሐማት፣ ከሴፈርዋይም ከተሞች አምጥቶ በእስራኤላውያን ቦታ እንዲገቡ በሰማርያ ከተሞች አሰፈራቸው፤ እነርሱም ሰማርያን ወርሰው በከተሞቿ ይኖሩ ጀመር።
በዚህ ጊዜ በኤፍራጥስ ማዶ ገዥ የነበረው ተንትናይ፣ ሰተርቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው ሄደው፣ “ይህን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራትና ውቅሩንም ለመጠገን የፈቀደላችሁ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው።
በኤፍራጥስ ማዶ ገዥ የነበረው ተንትናይ፣ ሰተርቡዝናይ፣ ተባባሪዎቻቸውና በኤፍራጥስ ማዶ የነበሩ ሹማምት ለንጉሥ ዳርዮስ የላኩት ደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤
አሁንም በኤፍራጥስ ማዶ አገረ ገዥ የሆንኸው ተንትናይ፣ ሰተርቡዝናይና እናንተም በዚያ አውራጃ የምትገኙ ተባባሪዎቻቸው ሁሉ ወደዚያ አትድረሱ።
በተባባሪዎቹና በሰማርያ ሰራዊት ፊት፣ “እነዚህ ደካማ አይሁድ ምን እያደረጉ ነው? ቅጥራቸውን መልሰው ሊሠሩ ነውን? መሥዋዕት ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት ጀንበር ሠርተው ሊጨርሱ ነውን? እንደዚያ ተቃጥሎ የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን?” አለ።
እነዚህን ሁሉ ቈንጆ ልጃገረዶች በሱሳ ግንብ ወደሚገኘው ልዩ የሴቶች መኖሪያ ቦታ እንዲያመጡ፣ ንጉሡ በግዛቱ በሚገኙት አውራጃዎቹ ሁሉ ባለሥልጣኖችን ይሹም፤ እነርሱም የሴቶች የበላይ ኀላፊ በሆነው በንጉሡ ጃንደረባ በሄጌ ኀላፊነት ሥር ይሁኑ፤ የውበትም እንክብካቤ ይደረግላቸው።
የሚያስጨንቅ ራእይ አየሁ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ ዘራፊ ይዘርፋል። ኤላም ሆይ፤ ተነሺ፤ ሜዶን ሆይ፤ ክበቢ፤ እርሷ ያደረሰችውን ሥቃይ ሁሉ አስቀራለሁ።
“ኤላም በዚያ አለች፤ ሰራዊቷም ሁሉ በመቃብሯ ዙሪያ አለ፤ ሁሉም ታርደዋል፤ በሰይፍ ወድቀዋል። በሕያዋን ምድር ሽብር የነዙ ሁሉ ሳይገረዙ ከምድር በታች ወርደዋል፤ ወደ ጕድጓድ ከወረዱት ጋራ ዕፍረታቸውን ተሸክመዋል፤