ዘፀአት 2:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅርጫቱን ስትከፍተው ሕፃኑን በውስጡ አየች፤ ያለቅስ ስለ ነበርም ዐዘነችለትና፣ “ከዕብራውያን ሕፃናት አንዱ መሆን አለበት” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከፈተችውም ጊዜ ሕፃኑን አየች፥ እነሆም ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፤ አዘነችለትም፦ “ይህ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከፈተችውም ጊዜ አንድ ሕፃን በውስጡ አገኘች፤ ሕፃኑም ያለቅስ ስለ ነበር አዘነችለትና “ይህ ከዕብራውያን ሕፃናት አንዱ ነው” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሣጥኑን በከፈተችም ጊዜ ሕፃኑን አየች፤ እነሆም፥ ሕፃኑ በሣጥኑ ውስጥ ያለቅስ ነበር፤ የፈርዖንም ልጅ አዘነችለት፥ “ይህ ሕፃን ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከፈተችውም ጊዜ ሕፃኑን አየች፤ እነሆም ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፤ አዘነችለትም፤ “ይህ ከዕብራውያን ልጆች አንድ ነው፤” አለች። |
ጌታ ሆይ፤ የባሪያህን ጸሎት፣ ስምህን በመፍራት ደስ የሚሰኙትን የባሪያዎችህንም ጸሎት ጆሮህ ታድምጥ። በዚህ ሰው ፊት ሞገስን አድርገህለት ዛሬ ለባሪያህ መከናወንን ስጠው።” በዚያ ጊዜ እኔ የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።
በዚህ ጊዜ የፈርዖን ልጅ ልትታጠብ ወደ አባይ ወንዝ ወረደች፤ በምትታጠብበትም ጊዜ ደንገጥሮቿ በወንዙ ዳር ወዲያና ወዲህ ይሉ ነበር፤ በቄጠማውም መካከል የተቀመጠ ቅርጫት አይታ ከደንገጥሮቿ አንዷን እንድታመጣው ላከቻት።
እያንዳንዱ ሰው፣ ዕብራዊ የሆነውን ወንድ ባሪያውንና ዕብራዊት የሆነችውን ሴት ባሪያውን ነጻ ማውጣት ነበረበት፤ ማንም ሰው አይሁዳዊ ወንድሙን በባርነት መግዛት አልነበረበትም።