ዘፀአት 13:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ በዚች ዕለት በአቢብ ወር ወጥታችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ዛሬ በአቢብ ወር ወጥታችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ቀን፥ የዓመቱ መጀመሪያ በሆነው በአቢብ ወር ግብጽን ለቃችሁ ወጥታችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በዚች ቀን በሚያዝያ ወር ወጥታችኋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ዛሬ በአቢብ ወር ወጥታችኋል። |
“የቂጣ በዓልን አክብር፤ እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን እርሾ የሌለውን ቂጣ ብላ፤ ይህንም በአቢብ ወር በተወሰነ ቀን አድርግ፤ በዚያ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና። “ማንም በፊቴ ባዶ እጁን አይቅረብ።
“የቂጣን በዓል አክብር። እንዳዘዝሁህም ለሰባት ቀን ቂጣ ብላ፤ ይህንም በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር አድርግ፤ በዚያ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና።