ዘፀአት 1:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፤ እስራኤላውያን በቍጥር በልጠውናል፤ ከእኛም ይልቅ እየበረቱ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ሕዝብ ከእኛ ይልቅ በዝተዋል በርትተውማል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “እነሆ፥ እነዚህ እስራኤላውያን ቊጥራቸው በዝቶአል፤ የኀይላቸውም ብርታት አስጊ ሆኖብናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ሕዝቡን፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሕዝብ ታላቅና ብዙ ሆነዋል፤ ከእኛም ይልቅ በርትተዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ሕዝቡን፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከእኛ ይልቅ በዝተዋል በርትተውማል፤ |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የአባትህ አምላክ ነኝ፤ ወደ ግብጽ ለመውረድ አትፍራ፤ በዚያ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና፤
እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
ቀደም ሲል እኛ ራሳችን ማስተዋል የጐደለን፣ የማንታዘዝ፣ የተታለልን፣ ለተለያየ ምኞትና ምቾት ባሪያ ሆነን የተገዛን ነበርን፤ እየተጣላንና እርስ በርስ እየተጠላላን በክፋትና በምቀኛነት እንኖር ነበር።