ኤፌሶን 6:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእኛን ሁኔታ እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያበረታ ለዚሁ ስል ወደ እናንተ እልከዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እኛ ሁኔታ እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያጽናና ወደ እናንተ የምልከው በዚህ ምክንያት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እኛ እንዴት እንደ ሆንን እንድታውቁና እናንተንም እንዲያበረታታችሁ በማለት እርሱን ወደ እናንተ ልኬዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዜናዬን ታውቁ ዘንድ፥ ልባችሁም ይጽናና ዘንድ፥ ስለዚህ ወደ እናንተ ላክሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወሬአችንን እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያጽናና ወደ እናንተ የምልከው ስለዚህ ምክንያት ነው። |
እንዲሁም ወንድሜን፣ ዐብሮ ሠራተኛዬና ዐብሮኝ ወታደር የሆነውን፣ በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲንከባከበኝ የላካችሁትን፣ የእናንተ መልእክተኛ የሆነውና አገልጋዩን አፍሮዲጡን መልሼ እንድልክላችሁ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ደግሞም ልባቸው እንዲጽናናና በፍቅር እንዲተሳሰሩ፣ ፍጹም የሆነውን የመረዳት ብልጽግና አግኝተው የእግዚአብሔር ምስጢር የሆነውን ክርስቶስን እንዲያውቁ እተጋለሁ፤
በእምነታችሁ እንዲያጸናችሁና እንዲያበረታችሁ ወንድማችንንና በክርስቶስ ወንጌል ሥራ ከእኛ ጋራ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤