ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በእግዚአብሔር ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፣ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን ከሞት አተረፈ።
መክብብ 8:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአምላክ ፊት መሐላ ስለ ፈጸምህ፣ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር እልሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ፦ በመለኮታዊ መሐላ መሠረት የንጉሥን ትእዛዝ ጠብቅ እልሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለንጉሡ እታዘዛለሁ ብለህ በመሐላ ለእግዚአብሔር ቃል ስለ ገባህ ለንጉሥ ታማኝ ሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ የንጉሥን አፍ ጠብቅ፤ ለመሐላ ቃልም አትቸኩል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ፦ በእግዚአብሔር መሐላ ምክንያት የንጉሥን ትእዛዝ ጠብቅ እልሃለሁ። |
ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በእግዚአብሔር ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፣ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን ከሞት አተረፈ።
በሁለቱ መካከል ያለው አለመግባባት መፍትሒ የሚያገኘው፣ ጎረቤቱ የሌላውን ሰው ንብረት እንዳልወሰደ በእግዚአብሔር ፊት በመማል ነው። ባለቤቱም ይህን መቀበል አለበት፤ የካሳም ክፍያ አይጠየቅም።
ሕዝቡ ወደ ጫካው በገባ ጊዜ፣ የማሩ ወለላ እየተንጠባጠበ መውረዱን አየ፤ ሆኖም መሐላውን ፈርቶ ስለ ነበር፣ እጁን ወደ አፉ የዘረጋ ማንም አልነበረም።