ከተሞቹን ደመሰሱ፤ መልካሙን የዕርሻ መሬት ሁሉ እስኪሸፍነው ድረስ፣ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ድንጋይ ጣለበት፤ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤ ጥሩ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቈርጠው ጣሉ። ቂርሐራሴት ብቻ ከነድንጋይዋ ቀርታ ነበር፤ እርሷንም ቢሆን ባለወንጭፉ ሰራዊት ከብቦ አደጋ ጣለባት።
መክብብ 3:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንጋይን ለመበተን ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፥ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንጋይ ለመበተን ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለማቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንጋይን ለመወርወር ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋይን ለመጣል ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፥ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፥ |
ከተሞቹን ደመሰሱ፤ መልካሙን የዕርሻ መሬት ሁሉ እስኪሸፍነው ድረስ፣ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ድንጋይ ጣለበት፤ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤ ጥሩ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቈርጠው ጣሉ። ቂርሐራሴት ብቻ ከነድንጋይዋ ቀርታ ነበር፤ እርሷንም ቢሆን ባለወንጭፉ ሰራዊት ከብቦ አደጋ ጣለባት።
ሕዝቡን ሰብስቡ፤ ጉባኤውን ቀድሱ፤ ሽማግሌዎችን በአንድነት አቅርቡ፤ ሕፃናትን ሰብስቡ፤ ጡት የሚጠቡትንም አታስቀሩ፤ ሙሽራው እልፍኙን ይተው፣ ሙሽሪትም የጫጕላ ቤቷን ትተው።
በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፣ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ባለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደ ገና ዐብራችሁ ሁኑ።
ፀሓይ ለመጥለቅ በማዘቅዘቅ ላይ ሳለች ኢያሱ ትእዛዝ ሰጠ፤ ከዚያም የነገሥታቱን ሬሳ ከዛፎቹ ላይ አውርደው ቀድሞ ተደብቀው ወደ ነበሩበት ዋሻ ውስጥ ጣሏቸው። በዋሻውም አፍ ትልልቅ ድንጋዮች አኖሩ፤ ድንጋዮቹም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።