መክብብ 11:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናት ውሃ ካዘሉ፣ በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣ በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደመናት ዝናብ በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፥ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመና ብዙ ውሃ ባዘለ ጊዜ በምድር ላይ ያዘንበዋል፤ ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ በዚያው በወደቀበት ስፍራ ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናት ዝናም በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፤ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመናት ዝናብ በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፥ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል። |
የወይን አትክልት ሠራተኛውንም፣ ‘እነሆ፤ ፍሬ ለማግኘት ልፈልግባት ሦስት ዓመት ወደዚህች በለስ መጥቼ ምንም አላገኘሁም፤ ስለዚህ ቍረጣት፤ ለምን ዐፈሩን በከንቱ ታሟጥጣለች?’ አለው።