ዘዳግም 9:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አሮንን ሊያጠፋው ክፉኛ ተቈጥቶ ነበር፤ በዚያ ጊዜ ለአሮንም ጸለይሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አሮንንም እጅግ ተቆጥቶ ሊያጠፋው ስለ ነበር፥ በዚያን ጊዜ ስለ አሮንም ደግሞ ጸለይሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በአሮንም ላይ እጅግ ስለ ተቈጣ ሊገድለው ተቃርቦ ነበር፤ ስለዚህ በዚያው ጊዜ ለአሮንም ጭምር ጸለይኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አሮንን ሊያጠፋው እጅግ ተቈጣው፤ ስለ አሮንም ደግሞ በዚያን ጊዜ ጸለይሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አሮንን ሊያጠፋው እጅግ ተቆጣው፤ ስለ አሮንም ደግሞ በዚያን ጊዜ ጸለይሁ። |
ደግሞም ያን የኀጢአት ሥራችሁን፣ ያበጃችሁትን ጥጃ ወስጄ በእሳት አቃጠልሁት፤ ከዚያም ሰባብሬ እንደ ትቢያ ዱቄት እስኪሆን ድረስ ፈጭቼ ከተራራው በሚወርደው ጅረት ውስጥ በተንሁት።