ዘዳግም 6:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፣ “አምላካችን እግዚአብሔር ያዘዛችሁ የምስክርነቶቹ፣ የሥርዐቶቹና የሕጎቹ ትርጕም ምንድን ነው?” ብሎ በሚጠይቅህ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፥ ‘አምላካችን ጌታ ያዘዛችሁ ምስክርነቶች፥ ሥርዓት፥ ፍርድስ ምንድነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሚመጡት ዘመናት ልጅህ የእነዚህ ሕግጋት፥ ደንቦችና ሥርዓቶች ትርጒም ምንድን ነው ብሎ ሲጠይቅህ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነገ ልጅህ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ያዘዛችሁ ምስክርና ሥርዐት፥ ፍርድስ ምንድን ነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኋለኛው ዘመንም ልጅህ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ያዘዛችሁ ምስክርና ሥርዓት ፍርድስ ምንድር ነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥ |
ይኸውም ግብጻውያንን እንዴት አድርጌ እንደ ቀጣኋቸውና በመካከላቸውም ምልክቶቼን እንዴት እንዳደረግሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትነግሩና እኔ እግዚአብሔር መሆኔንም እንድታውቁ ነው።”
“በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፣ ‘ይህ ምን ማለት ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ እንዲህ በለው፤ ‘ከባርነት ምድር ከግብጽ እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ አወጣን፤
ዐይኖቻችሁ ያዩአቸውን ነገሮች እንዳትረሱ፣ ደግሞም በሕይወት እስካላችሁ ድረስ ከልባችሁ እንዳይጠፉ ብቻ ተጠንቀቁ፣ ነቅታችሁም ራሳችሁን ጠብቁ። እነዚህን ለልጆቻችሁና ከእነርሱ በኋላ ለሚወለዱት ልጆቻቸው አስተምሯቸው።