ዘዳግም 6:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማሳህ እንዳደረግኸው እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ ‘በማሳህ’ እንደ ፈተናችሁት ጌታ አምላካችሁን አትፈታተኑት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ማሳህ’ ተብሎ በሚጠራው ቦታ እንዳደረጋችሁት ዐይነት እግዚአብሔር አምላካችሁን አትፈታተኑ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በፈተና ቀን እንደ ፈተንኸው አምላክህ እግዚአብሔርን አትፈታተነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማሳህ እንደ ፈተናችሁት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አትፈታተኑት። |
ስለዚህ፣ “የምንጠጣውን ውሃ ስጠን” በማለት ሙሴን ተጣሉት። ሙሴም፣ “እኔን ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አለ።
ስፍራውንም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን ተፈታትነዋልና።
ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “ቱሚምህና ኡሪምህ፣ ለምታምነው ሰው ይሁን፤ ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤ በመሪባም ውሃ ከርሱ ጋራ ተከራከርህ።