የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይሥሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ሐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው።
ዘዳግም 5:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ ለእነርሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም እንዲሆንላቸው፣ እኔን እንዲፈሩና ሁልጊዜ ትእዛዞቼን ሁሉ እንዲጠብቁ እንደዚህ ያለ ልብ ቢኖራቸው ምናለ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁልጊዜ በዚህ ዐይነት ቢያስቡማ እንዴት መልካም ነበር! ሁልጊዜ ቢያከብሩኝና ትእዛዞቼንም ሁሉ ቢፈጽሙ ሁሉ ነገር ለእነርሱና ለዘሮቻቸው ለዘለዓለም በመልካም ሁኔታ በተከናወነላቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእነርሱ፥ ለዘለዓለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ እንዲጠብቁ እንዲህ ያለ ልብ ማን በሰጣቸው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእነርሱ ለዘላለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ እንዲጠብቁ እንዲህ ያለ ልብ ምነው በሆነላቸው! |
የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይሥሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ሐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው።
አምላካችንን እግዚአብሔርን በመታዘዝ መልካም ይሆንልን ዘንድ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንታዘዛለን።”
“ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ፤ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈቀዳችሁም፤
ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋራ ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን።
አሁንም እስራኤል ሆይ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትፈራው፣ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ፣ እንድትወድደው፣ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ እንድታገለግለው፣
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፣ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ለዘላለም መልካም እንዲሆንላችሁ፣ እኔ የምሰጥህን እነዚህን ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ፈጽማቸው።
“በምድሪቱ በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ እኔን ማክበር እንዲማሩ፣ ለልጆቻቸውም እንዲያስተምሩ ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ሕዝቡን በፊቴ ሰብስብ” ባለኝ ጊዜ፣ በኮሬብ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቆማችሁበትን ዕለት አስታውሱ።
ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ለዘላለም በሚሰጥህም ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፣ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ሥርዐቱንና ሕግጋቱን ጠብቅ።
አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።
በምትወርሷት ምድር በሕይወት ለመኖር እንድትችሉ፣ መልካም እንዲሆንላችሁና ዕድሜያችሁም እንዲረዝም፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።
መልካም እንዲሆንልህና እግዚአብሔር ለአባቶችህ በመሐላ እንድትወርሳት፣ በእግዚአብሔር ፊት ተስፋ የሰጣቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ ቀናና መልካም የሆነውን አድርግ፤
እንግዲህ እስራኤል ሆይ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት በምታፈስሰው ምድር መልካም እንዲሆንልህና እጅግ እንድትበዛ፣ ትእዛዙንም ትጠብቅ ዘንድ ጥንቃቄ አድርግ።
የሚናገረውን እርሱን እንቢ እንዳትሉት ተጠንቀቁ። እነዚያ ከምድር ሆኖ ሲያስጠነቅቃቸው የነበረውን እንቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፣ እኛ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ከርሱ ብንርቅ እንዴት ልናመልጥ እንችላለን?