ዘዳግም 31:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው፣ እነዚህንም ያጠፋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው እነዚህንም ያጠፋቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የአሞራውያንን ነገሥታት ሲሖንንና ዖግን ድል ነሥቶ አገራቸውን እንዳጠፋ ሁሉ በእነርሱም ላይ እንዲሁ ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም ባጠፋቸው በዮርዳኖስ ማዶ በሚኖሩ በሁለቱ በአሞሬዎናውያን ነገሥታት በሴዎንና በዐግ፥ በምድራቸውም እንዳደረገ እንዲሁ ያደርግባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ባጠፋቸው በአሞራውያን ነገሥታት በሴዎንና በዐግ በምድራቸውም እንዳደረገ ያደርግባቸዋል። |
በዚያ ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ስል አዘዝሁት፤ “አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ በገዛ ዐይንህ አይተሃል፤ አሁንም ዐልፈህ በምትሄድባቸው መንግሥታት ላይ ሁሉ እግዚአብሔር ይህንኑ ይደግመዋል።
አምላክህ እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ምድራቸውን ትወርሳለህ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው፣ ኢያሱም አንተን ቀድሞ ይሻገራል።
አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥህን ሕዝቦች ሁሉ ማጥፋት አለብህ፤ አትዘንላቸው፤ ወጥመድ ስለሚሆኑብህም አማልክታቸውን አታምልክ።
አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጠህና አንተም ድል ባደረግሃቸው ጊዜ፣ ሁሉንም ፈጽመህ ደምስሳቸው፤ ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፤ አትራራላቸውም።
በፊታችሁ ተርብ ላክሁ፤ ይህም እነርሱንና ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ጭምር ከፊታችሁ አሳደደ፤ ይህ ደግሞ በራሳችሁ ሰይፍና ቀስት ያደረጋችሁት አይደለም።