ዘዳግም 25:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እህል በምታበራይበት ጊዜ የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እህልህን በምታበራይ ጊዜ በሬዉን አፉን አትሰረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እህል የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። |
ኤፍሬም ማበራየት እንደምትወድድ፣ እንደ ተገራች ጊደር ነው፤ በተዋበ ጫንቃዋም ላይ፣ ቀንበርን አኖራለሁ፤ ኤፍሬምን እጠምዳለሁ፤ ይሁዳ ያርሳል፤ ያዕቆብም መሬቱን ያለሰልሳል።