ዘዳግም 23:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደስ በሚያሠኘው ቦታና ራሱ በመረጠው ከተማ በመካከልህ ይኑር፤ አንተም አታስጨንቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከደጆችህ በሚመርጣት በአንዲቱ በሚወድዳት ስፍራ ከአንተ ጋር በመካከልህ ይቀመጥ፥ አንተም አታስጨንቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከከተሞችህ በአንዱ በመረጠው ስፍራ ከአንተ ጋር በመካከልህ ይኑር እንጂ አታስጨንቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአንተ ጋር ይኑር፤ በመካከልህም በሚወድዳት በአንዲቱ ስፍራ ይቀመጥ፤ አንተም አታስጨንቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደጆችህ በሚመርጣት በአንዲቱ በሚወድዳት ስፍራ ከአንተ ጋር በመካከልህ ይቀመጥ፥ አንተም አታስጨንቀው። |
“ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።