ዘዳግም 20:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ አለዚያ በጦርነቱ ይሞትና ሌላ ሰው ያገባታል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ይሞትና ሌላ ሰው ያገባታል።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስት ለማግባትስ ልጃገረድ ያጨ ሰው አለን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ ያለበለዚያ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት እርሱ ያጫት ልጃገረድ ለሌላ ሰው ሚስት ትሆናለች።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚስትም አጭቶ ያላገባት ሰው ቢኖር በጦርነት እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያገባት ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚስትም አጭቶ ያላገባትም ሰው ቢኖር በሰልፍ እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያገባት ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። |
አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፣ ለጦርነት አይሂድ፤ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሠራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ ቤቱ ይቈይ፤ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።
ሚስት ለማግባት ልጃገረድ ታጫለህ፤ ሌላው ግን ወስዶ ይደፍራታል። ቤት ትሠራለህ፣ ግን አትኖርበትም። ወይን ትተክላለህ፤ ፍሬውን ግን አትበላም።