ዘዳግም 2:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ አምላካችን እግዚአብሔር በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፣ ወደ ማንኛውም የአሞናውያን ምድር ወይም በያቦቅ ወንዝ መውረጃ ወዳለው ምድር ወይም ደግሞ በኰረብቶች ወዳሉት ከተሞች ዙሪያ ዐልፋችሁ አልሄዳችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብቻ ጌታ አምላካችን ወደ ከለከለን፥ ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማውም አገር ወዳሉት ከተሞች አልቀረብንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ወደ ዐሞናውያን ግዛት አጠገብ ወይም ወደ ያቦቅ ወንዝ ዳርቻ ወይም ወደ ኮረብታማይቱ አገር ከተሞች ወይም እግዚአብሔር እንዳንደርስባቸው ወዳዘዘን እነዚህን ከመሳሰሉት አገሮች ወደ አንዲቱ እንኳ አልቀረብንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተራራማውም ሀገር ወደ አሉ ከተሞች አልደረስንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ወደ ከለከለን ሁሉ፥ ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማውም አገር ወዳሉት ከተሞች አልደረስንም። |
እስራኤል ግን በሰይፍ መታው፤ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ድረስ ያለውንም ምድሩን ወሰደበት፤ ይሁን እንጂ የአሞናውያን ወሰን የተመሸገ ስለ ነበር ከያቦቅ አላለፈም።
ከየትኛውም የአሞናውያን ምድር ለእናንተ ርስት ስለማልሰጣችሁ፣ አሞናውያን ዘንድ በደረሳችሁ ጊዜ አታስቸግሯቸው፤ ለጦርነትም አታነሣሧቸው። ያን ቦታ ርስት አድርጌ ለሎጥ ዘሮች ሰጥቻቸዋለሁ።”
ከየትኛውም ምድራቸው ላይ ለጫማችሁ መርገጫ ታኽል እንኳ መሬት ስለማልሰጣችሁ፣ ለጦርነት አታነሣሧቸው። ኰረብታማውን የሴይርን አገር ርስት አድርጌ ለዔሳው ሰጥቼዋለሁ።
ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሞዓባውያን ምድር አንዳችም መሬት ስለማልሰጣችሁ አታስቸግሯቸው፤ ለጦርነትም አታነሣሧቸው፤ ዔርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ” አለኝ።
ነገር ግን የሸለቆውን እኩሌታ ወሰን በማድረግ ከገለዓድ አንሥቶ እስከ አርኖን ሸለቆ፣ ከዚያም የአሞናውያን ድንበር እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ያለውን ግዛት ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው።
መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፣ ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ላይ ካለችው ከአሮዔር ማለት ከሸለቆው መካከል አንሥቶ፣ የአሞናውያን ወሰን እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ገዝቷል፤ ይህም የገለዓድን እኩሌታ ይጨምራል።