ዘዳግም 2:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰፈር ፈጽሞ እስኪያጠፋቸውም ድረስ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰፈሩበትም መካከል አልቀው እስኪጠፉ ድረስ የጌታ እጅ በላያቸው ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በሙሉ እስኪደመስሳቸው ድረስ እነርሱን ከመቃወም አልተመለሰም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰፈርም መካከል ተለይተው እስኪጠፉ ድረስ የእግዚአብሔር እጅ በላያቸው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰፈርም መካከል ተቈርጠው እስኪጠፉ ድረስ የእግዚአብሔር እጅ በላያቸው ነበረ። |
ይህን ስታዩ፣ ልባችሁ ሐሤት ያደርጋል፤ ዐጥንቶቻችሁም እንደ ሣር ይለመልማሉ፤ የእግዚአብሔር እጅ ከባሮቹ ጋራ መሆኑ ይታወቃል፤ ቍጣው ግን በጠላቶቹ ላይ ይገለጣል።
ምንም እንኳ አስቀድማችሁ ይህን ሁሉ የምታውቁ ቢሆንም፣ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ ምድር እንዴት እንዳወጣ፣ በኋላ ግን ያላመኑትን እንዳጠፋ ላስታውሳችሁ እወድዳለሁ።
እስራኤላውያን ለውጊያ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር አስቀድሞ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረውና እንደ ማለው ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ ትከፋባቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እጅግ ተጨነቁ።
የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፣ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዦች በሙሉ ጠርተው፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ አለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ።
ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱት በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በዕባጭ መታ።
በዚህ ሁኔታ ፍልስጥኤማውያን ድል ስለ ተመቱ፣ የእስራኤልን ምድር ዳግመኛ አልወረሩም። ሳሙኤል በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር።