ዘዳግም 19:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፤ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፤ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገዳዩ የሚኖርበት ከተማ መሪዎች ሰው በመላክ እነርሱም ነፍሰ ገዳዩን አስመጥተው የሟቹን ደም ለመበቀል መብት ላለው የቅርብ ዘመዱ አሳልፈው ይስጡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከተማው ሽማግሌዎች ይልካሉ፤ ከዚያም ይይዙታል። በባለደሙም እጅ አሳልፈው ይሰጡታል፤ ይሞታልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከተማው ሽማግሌዎች ይልካሉ፥ ከተማጠነበትም ከተማ ይነጥቁታል፥ እንዲሞትም በደም ተበቃዩ እጅ አሳልፈው ይሰጡታል። |
እነሆ ቤተ ዘመዱ ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሥተው፣ ‘ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለንና ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፣ ከዚያም ወራሽ አልባ ትሆኛለሽ’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን አጥፍተው፣ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”