ዘዳግም 18:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም ሰው ነቢዩ በስሜ የሚናገረውን ቃሌን ባይሰማ፣ እኔ ራሴ በተጠያቂነት እይዘዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሰው ነቢዩ በስሜ የሚናገረውን ቃሌን ባይሰማ፥ እኔ ራሴ በተጠያቂነት እይዘዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ስም የሚናገረውን የዚያን ነቢይ ቃል የማይሰማ ሁሉ እቀጣዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስሜም በሚናገረው ሁሉ ያን ነቢይ የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀለዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስሜም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለሁ። |
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ ድነት ቸል ብንል እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ ድነት በመጀመሪያ በጌታ ተነገረ፤ ከርሱ የሰሙትም ለእኛ አረጋገጡልን።
መሠዊያውን የሠራነው እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ ለማለት፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ልናሳርግበት ወይም የኅብረት መሥዋዕት ልናቀርብበት አስበን ከሆነ፣ ራሱ እግዚአብሔር ይበቀለን።