ዘዳግም 17:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፣ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፣ “በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፣ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ” ብትል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፥ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፥ ‘በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፥ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ ወደሚሰጥህ ምድር በመግባት ምድሩን ወርሰህ ከተደላደልክ በኋላ በዙሪያዬ እንዳሉት ሕዝቦች ንጉሥ ላንግሥ ብትል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ፦ በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ እሾማለሁ ብትል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ፦ በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ ንጉሥ አነግሣለሁ ስትል፥ |
አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር በሚያመጣህና ብዙዎችን ከአንተ የሚበልጡ ታላላቆችና ብርቱዎች የሆኑትን ሰባቱን አሕዛብ፦ ኬጢያውያንን፤ ጌርጌሳውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ በሚያስወጣቸው ጊዜ፣
ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ እነርሱም ምድሪቱን ወረሱ፣ መኖሪያቸውም አደረጓት።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ንቃችሁ፤ ‘የለም፤ ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ። ስለዚህ በየነገዳችሁና በየጐሣችሁ ሆናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቅረቡ።”
ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ወግና ሥርዐት ለሕዝቡ ገልጾ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ።
ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፣ “ሌላው በደላችን ሳያንስ፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ክፋት ስላደረግን እንዳንሞት፣ ለአገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት።
እንዲህም አለ፤ “በላያችሁ የሚነግሠው ንጉሥ የሚያደርግባችሁ ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሠረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ።