ዘዳግም 15:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን አገልጋይህ፣ አንተንና ቤተ ሰብህን ከመውደዱና ከአንተም ጋራ ደስተኛ ሆኖ ከመኖሩ የተነሣ፣ “ከአንተ መለየት አልፈልግም” ቢልህ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን አገልጋይህ፥ አንተንና ቤተሰብህን ከመውደዱና ከአንተም ጋር ደስተኛ ከመሆኑ የተነሣ፥ ከአንተ መለየት አልፈልግም ቢልህ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን ባሪያህ አንተንና ቤተሰብህን በመውደዱና ከአንተም ጋር ስምምነት ስላለው ለመሄድ አይፈልግም ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን አንተንና ቤትህን ስለ ወደደ፥ በአንተም ዘንድ መኖር መልካም ስለሆነለት፦ ‘አልወጣም’ ቢል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን አንተንና ቤትህን ስለወደደ፥ ከአንተም ጋር መልካም ስለ ሆነለት፦ ልወጣ አልወድድም ቢል፥ |
አንተም ራስህ በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርህና አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ይህን ትእዛዝ ዛሬ የምሰጥህም በዚሁ ምክንያት ነው።
ጆሮውን ከቤትህ መዝጊያ ላይ በማስደገፍ በወስፌ ትበሳዋለህ፤ ከዚያም ዕድሜ ዘመኑን አገልጋይህ ይሆናል። በሴት አገልጋይህም ላይ እንደዚሁ አድርግ።