ዘዳግም 14:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሣማም እንደዚሁ ርኩስ ነው፤ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም፣ ስለማያመሰኳ፣ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥንባቸውንም አትንኩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሣማም፥ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኩህ፥ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥምባቸውንም አትንኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሣማዎችን አትብሉ፤ እነርሱ ሰኮናቸው የተከፈለ ቢሆንም ስለማያመሰኩ የረከሱ ሆነው ይቈጠራሉ፤ እንደነዚህ ያሉትን እንስሶች መብላት ይቅርና በድናቸውን እንኳ አትንኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርያም፥ ሰኰናው ስለተሰነጠቀ፥ ጥፍሩም ከሁለት ስለተከፈለ፥ ነገር ግን ሰለማያመሰኳ፥ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋዉን አትብሉ፤ በድኑንም አትንኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስላላመሰኳ፥ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋውን አትብሉ፥ በድኑንም አትንኩ። |
“ወደ አትክልት ቦታዎች ለመሄድና ከተክሎቹ አንዱን ለማምለክ ራሳቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የዕሪያዎችንና የዐይጦችን ሥጋ፣ የረከሱ ነገሮችንም የሚበሉ ሁሉ የመጨረሻ ፍርዳቸውን በአንድነት ይቀበላሉ” ይላል እግዚአብሔር።
ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል።
“ ‘ማንኛውም ሰው ሳያውቅ በሥርዐቱ መሠረት የተከለከለውን ርኩስ ነገር ቢነካ፣ ይኸውም፦ የረከሰ የአውሬ በድን ወይም የረከሰ የቤት እንስሳ በድን ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚንቀሳቀሰውን የረከሰ ፍጥረት በድን ቢነካ ይህ ሰው ረክሷል፤ በደለኛም ነው።
ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፣ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ እነርሱ ቢያመሰኩ እንኳ፣ ሰኰናቸው የተሰነጠቀ ባለመሆኑ፣ በሥርዐቱ መሠረት በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።