La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 11:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፥ መንገድ ስትሄድ፥ ስትተኛና ስትነሣ ስለዚህ አጫውታቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤ በቤት በምትቀመጡበት ጊዜ፥ ወይም ስትሄዱ፥ ዕረፍት በምታደርጉበትም ሆነ በምትሠሩበት ጊዜ ሁሉ ስለ እነርሱ ተነጋገሩ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ በቤ​ትም ሲቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም ሲሄዱ፥ ሲተ​ኙም፥ ሲነ​ሡም እን​ዲ​ነ​ጋ​ገ​ሩ​በት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ልጆቻችሁንም አስተምሩአቸው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም ስትነሣም አጫውቱአቸው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 11:19
12 Referencias Cruzadas  

እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፣ ከልቦናቸውም ቃልን የሚያወጡ አይደሉምን?


ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።


እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን።


ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ብትቀበል፣ ትእዛዜንም በልብህ ብታኖር፣


ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤ በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።


እኔ ዛሬ እንደማደርገው፣ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል። ስለ አንተ ታማኝነትም፣ አባቶች ለልጆቻቸው ይነግራሉ።


አባቶች ሆይ፤ እናንተም ልጆቻችሁን አታስቈጧቸው፤ ነገር ግን በጌታ ምክርና ተግሣጽ አሳድጓቸው።


እንዲህ አላቸው፤ “የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዝዟቸው፣ እኔ ዛሬ በግልጽ የምነግራችሁን ቃሎች ሁሉ በልባችሁ አኑሩ።


ለልጆችህም አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።