“ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፣ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፣ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክታቸውን ከፊቱ አሳድዶ ታላላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?
ዘዳግም 10:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ውዳሴህ ነው፤ በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን፣ እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ያደረገልህ አምላክህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቅና የሚያስፈሩ ነገሮችን ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱ አምላክህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ አምላክህ ነው፤ እርሱ ለአንተ ያደረገልህን ታላላቅና አስደናቂ ነገሮችን ሁሉ በገዛ ዐይኖችህ ስላየህ ዘወትር አመስግነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይኖችህ ያዩአቸውን እነዚህን ታላላቆች የከበሩትን ነገሮች ያደረገልህ እርሱ መመኪያችሁ ነው፤ እርሱም አምላክህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቆች የሚያስፈሩትንም ነገሮች ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱም አምላክህ ነው። |
“ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፣ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፣ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክታቸውን ከፊቱ አሳድዶ ታላላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?
“እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ከአንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ ቀደም በዓለም ሁሉ ለየትኛውም ሕዝብ ከቶ ያልተደረገ፣ በሕዝብህ ሁሉ ፊት ድንቅ አደርጋለሁ፤ በመካከላቸው ዐብረሃቸው የምትኖር ሕዝብ እኔ እግዚአብሔር ለአንተ የማደርግልህ ሥራ የቱን ያህል አስፈሪ እንደ ሆነ ያያሉ።
ከእንግዲህ በቀን የፀሓይ ብርሃን አያስፈልግሽም፤ በሌሊትም የጨረቃ ብርሃን አያበራልሽም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃን፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና።
እንዲሁም እግዚአብሔር በምድሪቱ የሚኖሩትን አሞራውያንን ጨምሮ ሕዝቦችን ሁሉ ከፊታችን አሳደደ፤ ስለዚህ እኛም እግዚአብሔርን እናመልካለን፤ አምላካችን ነውና።”