ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱ በዳዊት ሥርዐትም ይሄድ ነበር፤ ይሁን እንጂ፣ በኰረብታዎች ላይ መሥዋዕት ይሠዋና ዕጣን ያጥን ነበር።
ዘዳግም 10:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም እንዲሆንልህና ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞችና የእግዚአብሔር ሥርዐቶች እንድትጠብቅ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት እንድትጠብቅ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካምም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዐት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ፤ |
ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱ በዳዊት ሥርዐትም ይሄድ ነበር፤ ይሁን እንጂ፣ በኰረብታዎች ላይ መሥዋዕት ይሠዋና ዕጣን ያጥን ነበር።
አሁንም እስራኤል ሆይ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትፈራው፣ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ፣ እንድትወድደው፣ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ እንድታገለግለው፣
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ምን ጊዜም መልካም እንዲሆንልንና በሕይወት እንድንኖር ይህን ሥርዐት ሁሉ እንድንፈጽም፣ አምላካችንንም እግዚአብሔርን እንድንፈራ እግዚአብሔር አዘዘን።