ዘዳግም 1:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አላደመጣችሁም፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐምፃችሁ፣ በትዕቢታችሁ ወደ ተራራማው አገር ዘመታችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ተናገርኋችሁ፥ እናንተ ግን በጌታ ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ አልሰማችሁም፥ በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያለኝንም ለእናንተ ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እምቢተኞች ሆናችሁ፤ በእርሱም ላይ ዐምፃችሁ በትዕቢታችሁ ብዛት ወደ ኮረብታማይቱ አገር ዘመታችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ተናገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ተላለፋችሁ፤ በኀይላችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ተናገርኋችሁ፤ እናንተ ግን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ አልሰማችሁም፤ በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ። |
“ ‘ያገር ተወላጅም ይሁን መጻተኛ ሆነ ብሎ ኀጢአት የሚሠራ ማንኛውም ሰው ግን እግዚአብሔርን ስለሚያቃልል ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።