ቈላስይስ 3:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆች ሆይ፤ ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ በሁሉም ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆች ሆይ! ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆች ሆይ! ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ ስለ ሆነ በሁሉ ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆች ሆይ ለወላጆቻችሁ በሁሉ ታዘዙ፤ እንዲህ ማድረግ ይገባልና፤ ይህም እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆች ሆይ፥ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። |
እኛም አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ ፈጽመናል፤ እኛና ሚስቶቻችን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም የወይን ጠጅ ጠጥተን አናውቅም፤
“ልጅ አባቱን፣ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔ አባት ከሆንሁ፣ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ የት አለ?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ካህናት ሆይ፤ ስሜን የምታቃልሉት እናንተ ናችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘ስምህን ያቃለልነው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ።
አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።
የሚያስፈልገኝን ሁሉ፣ ከሚያስፈልገኝም በላይ ተቀብያለሁ፤ የላካችሁትንም ስጦታ ከአፍሮዲጡ እጅ ተቀብዬ ተሞልቻለሁ፤ ይህም መዐዛው የጣፈጠ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ነው።
የምንጸልየውም ለጌታ እንደሚገባ እንድትኖሩና በሁሉም ደስ እንድታሰኙት ነው፤ ይኸውም በመልካም ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ እግዚአብሔርን በማወቅ እያደጋችሁ፣
ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሠኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን። አሜን።