አሞጽ 9:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር፣ የሰራዊት ጌታ፣ ምድርን ይዳስሳል፤ እርሷም ትቀልጣለች፤ በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤ እንደ ግብጽ ወንዝም ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የሠራዊት አምላክ ምድርን ይዳስሳል እርሷም ትቀልጣለች፥ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፤ ሞላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ ትነሣለች፥ ዳግመኛም እንደ ግብጽ ወንዝ ትወርዳለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መላዋ ምድር እንደ ግብጹ የዐባይ ወንዝ ከፍና ዝቅ በማለት ትናወጣለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድሪቱን ሲነካ ትቀልጣለች፤ በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር ምድርን ሁሉ ይዳስሳል፤ ያነዋውጣታልም፤ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፤ ግድያ እንደ ወንዝ ይፈስሳል፤ ደግሞም እንደ ግብፅ ወንዝ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድርን ይዳስሳል እርስዋም ትቀልጣለች፥ የሚኖሩባትም ሁሉ ያለቅሳሉ፥ ሙላዋም እንደ ግብጽ ወንዝ ትነሣለች፥ ደግሞም እንደ ግብጽ ወንዝ ትወርዳለች። |
ምድሪቱ በዝናብ ዕጦት የምትጐዳው፣ የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው? ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ ደግሞም ሕዝቡ፣ “በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።
“በዚህ ነገር ምድር አትናወጥምን? በውስጧ የሚኖሩትስ ሁሉ አያለቅሱምን? የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤ እንደ ግብጽ ወንዝም ወደ ላይ ይፈናጠራል፤ ተመልሶም ይወርዳል።”