ከዚህ የተነሣም አሳ ባለራእዩን ተቈጣው፤ በጣም ስለ ተናደደም እስር ቤት አስገባው። በዚያ ጊዜም አሳ አንዳንድ ሰዎችን ክፉኛ አስጨነቃቸው።
አሞጽ 7:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሜስያስም፣ አሞጽን እንዲህ አለው፤ “አንተ ባለራእይ ከዚህ ሂድ! ከይሁዳ ምድር ሽሽ፤ እዚያም እንጀራህን ብላ፤ በዚያም ትንቢት ተናገር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሜስያስም አሞጽን እንዲህ አለው፦ “ባለ ራእዩ ሆይ! ሂድ ወደ ይሁዳም ምድር ሽሽ፥ በዚያም እንጀራን ብላ፥ በዚያም ትንቢትን ተናገር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሜስያስ አሞጽን እንዲህ አለው፦ “አንተ ባለ ራእይ! ወደ ይሁዳ ተመልሰህ ሂድና በዚያ ትንቢት እየተናገርክ መተዳደሪያህን አግኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሜስያስም አሞጽን፥ “ባለ ራእዩ ሆይ! ሂድ፤ ወደ ይሁዳ ምድር ሽሽ፤ በዚያም ተቀመጥ፥ በዚያም ትንቢትን ተናገር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሜስያስም አሞጽን፦ ባለ ራእዩ ሆይ፥ ሂድ ወደ ይሁዳም ምድር ሽሽ፥ በዚያም እንጀራን ብላ፥ |
ከዚህ የተነሣም አሳ ባለራእዩን ተቈጣው፤ በጣም ስለ ተናደደም እስር ቤት አስገባው። በዚያ ጊዜም አሳ አንዳንድ ሰዎችን ክፉኛ አስጨነቃቸው።
ባለራእዮችን፣ “ከእንግዲህ ራእይን አትዩ!” ይላሉ፤ ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤ “እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ ደስ የሚያሠኘውን ንገሩን፤ የሚያማልለውን ተንብዩልን።
እጅግ ሲበዛ ሆዳም ውሾች ናቸው፤ ጠገብሁን አያውቁም፤ የማያስተውሉ እረኞች ናቸው፤ ሁሉም በየራሳቸው መንገድ ሄዱ፤ እያንዳንዳቸውም የግል ጥቅማቸውን ፈለጉ።
ዕፍኝ ለማይሞላ ገብስና ለቍራሽ እንጀራ ስትሉ ሐሰትን የሚያደምጥ ሕዝቤን እየዋሻችሁ መሞት የማይገባውን በመግደል፣ መኖር የማይገባውንም በማትረፍ በሕዝቤ መካከል አርክሳችሁኛል።
“በመሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳት እንዳታነድዱ፣ ምነው ከእናንተ አንዱ የቤተ መቅደሱን ደጅ በዘጋ ኖሮ! እኔ በእናንተ ደስ አይለኝም፤ ከእጃችሁም ምንም ዐይነት ቍርባን አልቀበልም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የሚያገለግሉት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ሆድ ነው። በለሰለሰ አንደበታቸውና በሽንገላ የዋሆችን ያታልላሉ።
መንፈሳዊ ያልሆነ ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ የሆነውን ነገር ሊቀበል አይችልም፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለው ነገር ለርሱ ሞኝነት ነው፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ፣ ሊረዳው አይችልም።
በእናንተ ኀላፊነት ሥር ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቁትም ከእግዚአብሔር እንደሚጠበቅባችሁ በግድ ሳይሆን በፈቃደኝነት፣ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ጽኑ ፍላጎት ይሁን፤
ከዘሮችህም መካከል የተረፈው ማንኛውም ሰው፣ ለአንዲት ጥሬ ብርና ለቍራሽ እንጀራ ሲል በፊቱ ወድቆ ይሰግዳል፤ “የዕለት ጕርሴን እንዳገኝ እባክህ በማንኛውም የክህነት ሥራ ላይ መድበኝ” በማለት ይለምናል።’ ”
ቀደም ሲል በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፣ “ኑ ወደ ባለራእዩ እንሂድ” ይል ነበር፤ ዛሬ ነቢይ የሚባለው በዚያ ጊዜ ባለራእይ ይባል ነበርና።